ዋና ገጽ

01.

ሞቃታማ የኮምፖስት አዘገጃጀትና ኮምፖስት

ኮምፖስትን ማዘጋጀት ቀላል በሆነ አማርኛ ሲገለጽ የዕጽዋትና እንስሳት ቅሪተ ህያዋንን ስነ ህይወታዊ በሆነ መንገድ በማብላላት ለም ወደሆነ አፈር መቀየር ማለት ነው፣ ፣

ተጨማሪ ይመልከቱ
02.

የቨርሚኮምፖስት አዘገጃጀትና ቨርሚኮምፖስት

ቨርሚኮምፖስቲንግ (ቨርሚኮምፖስትን ማዘጋጀት) አንደኛው የኮምፖስት አዘገጃጀት ዘዴ ሲሆን. ተጨማሪ ይመልከቱ

ተጨማሪ ይመልከቱ
03.

ከኮምፖስት የሚዘጋጅ ፈሳሽ

ከኮምፖስት የሚዘጋጅ ፈሳሽ፣ ጥሩ የሆነ ኮምፖስትን ከውሃ ጋር አመጣጥኖ በመቀላቀል፣ የሚዘጋጅና እንደማዳበሪያነት የሚያገለግል እንዲሁም ተባይና በሽታን ለመከላከል ጥቅም ላይ የሚዉል ውህድ ነው፣ ፣.

ተጨማሪ ይመልከቱ
04.

በባዮ ኢንቴንሲቭ ዘዴና የተለያዩ እቃዎችን በመጠቀም ማምረት

ባዮ ኢንቴንሲቭ አመራረት ማለት፣ ኦርጋኒክ በሆነ የአመራረት መንገድ አነስተኛ ከሆነ ቦታ ላይ፣ የሚቻለዉን ያክል ከፍተኛ ምርት ማምረት የሚያስችል ዘዴ ነው፣ ፣..

ተጨማሪ ይመልከቱ

ስለኤደልማርክ

ኤደል ማርክ ሁለት የኖርዊያንኛ ቃላቶችን ማለትም ኤደልንና ማርክን በማገናኘት የተፈጠረ ስያሜ ነው፣ ፣ ኤደል ማለት እንደ እንቁ ከፍተኛ ዋጋ (ቫልዩ) ያለው ነገር ማለት ሲሆን ማርክ ደግሞ የመሬት ትል ማለት ነው፣፣ እነኝህን ሁለት ቃላቶች በማጣመር የተፈጠረው ኤደል ማርክ የሚለው ቃል በጥሬው ሲተረጎም፣ ከፍተኛ ዋጋ (ቫልዩ) ያለው የመሬት ትል እንደ ማለት ነው፣ ፣ ይህንን ስያሜ ለቀልዝ ትሎች መስጠት የቀልዝ ትሎቹ ከሚያበረክቱት አገልግሎት አንጻር ሲታይ ምናልባት ያንስባቸው ይሆናል እንጂ የሚበዛ አይደለም፣ ፣ ዋና ምክንያቱ ደግሞ እነኝህ የቀልዝ ትሎች ለሰው ልጅም ሆነ ሌሎች ፍጥረታት ህይወት በሚሰጡት አስደናቂ አገልግሎት ነው፣ ፣

በሂደት ላይ ያሎ ፕሮጀክቶች

ኤደልኮምፖስት

ኤደልኮምፖስት አነስተኛ የሆነና በግል እየተከናወነ ያለ የምርምር ፕሮጀክት ነው፣ ፣ ይህ ፕሮጀክት አነስተኛ በሆነ መጠን ቨርሚኮምፖስትን ለማዘጋጀት የሚያስችሉ ዘዴዎችን እንዲሁም የቨርሚኮምፖስትን ጥራት ከፍተኛ በማድረግ ስራ ላይ ያተኮረ ነው

ኤደል ጂዩስ

ይህም በተመሳሳይ መልኩ በግል እየተከናወነ ያለ የምርምር ፕሮጀክት ሲሆን ከቨርሚኮምፖስት ጥራት ያለዉና ደረጃዉን የጠበቀ ፍሳሽ (ወይንም ፈሳሽ ማዳበሪያ) በማበልሰግ ዙሪያ እየተከናወነ ያለ ነው፣ ፣

ኤደልፖኒክስ

ይህም እንደሌሎቹ ፕሮጀክቶች በግል እየተከናወነ ያለ የምርምር ፕሮጀክት ሲሆን፣ ከቨርሚኮምፖስት የሚዘጋጁ ፍሳሾችን በምን መልክ ለአትክልቶች ማብቀያነት ማዋል እንደሚቻል እየተሰራበት ያለ ፕሮጀክት ነው